Google ClassroomGoogle Classroom
GeoGebraGeoGebra Classroom

7.3 የጠጣር ምስሎች ባህሪያት (ጠርዝ፣ መለያያ እና ገጽ)

ከታች ባሉት ጠጣር ምስሎች ላይ ፦ - መለያያዎች (vertices) በነጠብጣብ ቀይ ቀለሞች ተወክለዋል። መለያያ ምንድን ነው? - ጠርዞች (edges) በሰማያዊ መስመሮች ተወክለዋል። ጠርዝን ምንድን ነው ? - ገጾች (faces) በቀለም በተቀቡ ንጣፎች ተወክለዋል። በቢጫ ቀለም የተቀቡት ንጣፎች የጎን ገጾች ሲሆኑ፣ በአረንጓዴ ቀለም የተቀቡት ደግሞ መሠረቶች (bases) ናቸው። መሠረቶች የገጽ ክፍል ናቸው። ገጾች እና መሠረቶች ምንድን ናቸው? መመሪያ፦ የእያንዳንዱን ምስል ጫፎች፣ ጠርዞች፣ ገጾች እና መሠረቶች በሙሉ ለማየት ምስሎቹን አሽከርክር/ሪ። ምስሎቹን ለማሽከርከር ማውዝህ/ሽ ከምስሉ አጠገብ እንጂ ምስሉ ላይ አለመሆኑን አረጋግጥ/ጪ። Author: Fishaw Mekash | Founder of Eduethiopia Contact: fishaw@eduethiopia.com Website: www.eduethiopia.com
ፍንጭ፦ የዚህ ፒራሚድ ገጾች (ከመሠረቱ በስተቀር) ሁሉም ሦስት ማዕዘኖች ሲሆኑ፣ የፒራሚዱ "ጫፍ" በሚመስለው ነጥብ ላይ አብረው ይገናኛሉ። መሠረቱን እንደ አንድ ገለልተኛ ገጽ አድርገህ/ሽ ልታስበው/ቢው ትችላለህ/ያለሽ፤ ምክንያቱም ልክ እንደሌሎቹ ገጾች ከአንድ ጫፍ ወይም መለያያ (vertex) ጋር አይገናኝም። ባለ ሦስት ማዕዘን ፒራሚዶች (Triangular pyramids) ልዩ ሁኔታ ያላቸው ሲሆኑ፣ በቴክኒክ ደረጃ ማናቸውንም ገጻቸውን እንደ መሠረት መጠቀም ይቻላል። _____________________________________________________________________________________________________
- ኮኖች (Cones)፣ ሲሊንደሮች (Cylinders) እና ስፌሮች (Spheres) ደግሞ ጠማማ ጠርዞች (curved edges) እና ጠማማ ገጾች (curved surfaces) አሏቸው። - ስፌር አንድ ጠማማ ገጽ ብቻ አለው። መሰረት የለውም። መለያያ የለውም። ጠርዝ የለውም። - ጠማማ ጠርዞች በብርቱካናማ ክቦች የሚወከሉ ሲሆን፣ ጠማማ ገጾች ደግሞ በሮዝ ቀለም በታጠፉ "ገጾች" ይወከላሉ። እያንዳንዳቸውን በራስህ/ሽ አገላለጽ እንዴት ትበይናለህ/ትበይኚያለሽ?
ስለ ጠጣር ምስሎች ምን ተገነዘባችሁ ?